Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Office of the Fire Marshal - Amharic

በእሳት ማርሻል ጽሕፈት-ቤት የእሳት መከላከል ክፍል፣ እሳት የመከላከል እና ከተማችን ውስጥ የሚኖሩ እና የሚሰሩ እንዲሁም ጉብኝት የሚያደርጉ ዜጎች እና ግለሰቦች ደህንነት የማረጋገጥ ግብን አንግቦ ይሰራል።

ይህንን ተልእኮ ለመወጣት፣ የእሳት መከላከል ደንቡ ላይ ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ፣ የእሳት ደህንነት ትምህርት መረጃ ማዳረስ፣ እሳት-ነክ መረጃ መሰብሰብ፣ ህንጻዎችን እና ስትራክቸሮችን መፈተሽ፣ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚከሰቱ እሳቶች መነሻቸውን እና መንስኤዎቻቸውን በትክክል ማወቅ፣ እና በእሳት አደጋ ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን ማሰር ያስፈልጋል።

ተልኳችንን በስኬት እንድንወጣ ከሁሉም የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የእሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች መምሪያ አባላት እገዛ ያስፈልገናል።

የእሳት መከላከል ክፍሉ የሚመራው በእሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ሀላፊ የእሳት ማርሻል ሆኖ እንዲሰራ በተሾመው ምክትል እሳት ሀላፊ ነው። ክፍሉ በአራት አበይት ቅርንጫፎች የተከፋፈለ ነው።

የአስተዳደር እገዛ አገልግሎቶች ቅርንጫፍ

ይህ ክፍል ለ FPD እንደ ምልመላ፣ የተጠቃሚ ክፍያዎች ሂሳብ መስራት፣ የተበየኑ ቅጣቶችን ማስኬድ፣ ወርሀዊ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት፣ የመዛግብት አያያዝ፣ የመረጃ ነጻነት ድንጋጌ ጥያቄዎች፣ የግለሰባዊ መዛግብት አቀማመጥ፣ እንዲሁም የሀገራዊ እሳት አደጋ ሪፖርቲንግ ስርአትን ማስተዳደር የመሳሰሉ እገዛዎች ያደርግለታል።

በተጨማሪም፣ ውሳኔ ሰጪ ሀላፊው ሁሉም በእሳት ደንቡ ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶች በአስተዳደራዊ ፍርድቤት ውሳኔ የማሰጠት ሀላፊነት አለበት።

ደንብ አስፈጻሚ ቅርንጫፍ

ይህ ቅርንጫፍ ወደ ስምንቱ የከተማዋ አቅጣጫዎች የተመደቡ የእሳት ፈታሾች አሉት። ሀላፊነቶቻቸውም የሚከተሉትን እና ሌሎችን ያጠቃልላሉ:

  • በፌደራል ባለቤትነት ስር ከሚገኙ ህንጻዎች እና ባለ አንድ ቤተሰብ ከሚኖርባቸው መኖሪያ ቤቶች ውጪ ሁሉም ህንጻዎች ላይ መደበኛ የጥገና ፍተሻዎችን ማካሄድ። አንድ ቤተሰብ ብቻ የሚኖርባቸው መኖሪያ ቤቶች የሚፈተሹት ጥያቄዎች ወይንም ቅሬታዎች ሲቀርቡ ብቻ ነው ።
  • ከእሳት ደንብ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን ማጣራት።
  • እንደ የጤና እንክብካቤ ተቋሞች፣ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ የማህበረሰብ መኖሪያ ተቋሞች፣ ወዘተ የመሳሰሉ የተመረጡ ይዞታዎች ላይ አመታዊ የፈቃድ እድሳት ፍተሻዎች ማድረግ።
  • የዲሲ መንግስታዊ ትምህርት-ቤቶች ፍተሻ።
  • ከዩናይትድ ስቴትስ ሚስጢራዊ አገልግሎት በሚቀርብ ጥያቄ መሰረት የፕሬዚዳንቱ እና ሌሎች ትላልቅ ባለስልጣናት የእሳት ደህንነት አገልግሎት መስጠት።
  • ፌስቲቫሎች እና ትላልቅ የህዝብ ስብሰባዎች ላይ የእሳት ደህንነት አገልግሎት መስጠት።
  • በሌሊት እና በቅዳሜና እሁዶች እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው የምሽት ክለቦች፣ ምግብ-ቤቶች እና ትያትሮች የመሳሰሉ የህዝብ መሰብሰቢያዎች ላይ የእሳት ፍተሻ አገልግሎት መስጠት።
  • በሌሊት እና በቅዳሜና እሁዶች እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው የምሽት ክለቦች፣ ምግብ-ቤቶች እና ትያትሮች የመሳሰሉ የህዝብ መሰብሰቢያዎች ላይ የእሳት ፍተሻ አገልግሎት መስጠት። Assigned to the Mayor’s Office of Community Relations and Services.

የቴክኒካዊ ፍተሻዎች እቅዶች እና የፈቃዶች ቅርንጫፎች

የቴክኒካዊ ፍተሻዎች እቅዶች እና የፈቃዶች ቅርንጫፎች የ ICC አለማቀፍ የእሳት ደንብ ላይ በተቀመጠው እና በ DCMR የእሳት ደንብ በተሻሻለው አሰራር መሰረት የስራ ፈቃዶች ላይ መካሄድ ያለባቸውን ልዩ ፍተሻዎች ያካሂዳል።

በተጨማሪ፣ የእቅዶች ግምገማ፣ የእሳት አደጋ ጊዜ ማስመለጫ እቅዶች ግምገማ፣ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታ ወይቨር ግምገማዎች፣ እና የሁልም ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ፕሮግራሞች እና አውደርእዮች ግምገማዎችን ያደርጋል። በደንቡ መሰረት መሰጠት ያለባቸው ሁሉም የስራ ፈቃዶች የመስጠት ሀላፊነት ያለው ይህ ቅርንጫፍ ነው።

ቅርንጫፉ የሚከተሉት ክፍሎችን ያጠቃልላል:

  • የጎጂ ማቴርያሎች ክፍል - ጎጂ ማቴርያሎች በሕገወጥ መንገድ መጣል እና ማፍሰስ፣ ታንከር አተካከል፣ ታንከር አወጋገድ፣ ፈንጂዎች፣ ርችቶች፣ ፓይሮቴክኒክስ፣ ጎጂ ማቴርያሎች ማከማቸት እና የነዳጅ ማደያ ጣብያዎችን ፍተሻ ያደርጋል።
  • የጤና እንክብካቤ ተቋማት ክፍል - የሆስፒታሎች፣ የነርሲንግ ቤቶች እና የተቋማዊ ሕክምና ድርጅቶች እንዲሁም የማህበረሰብ መኖሪያ ተቋሞች ፍተሻ አገልግሎት ይሰጣል።
  • የተቋማዊ ድርጅቶች ክፍል - የማረሚያ ቤት ተቋማት፣ የግማሽ መንገድ ቤቶች፣ የቀን እንክብካቤ ማእከሎች፣ የህጻናት እንክብካቤ ማእከሎች፣ ለህጻናት የማህበረሰብ መኖሪያ ተቋሞች ፣ እንዲሁም ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ፍተሻ ያደርጋል።

የእሳት ምርመራዎች ቅርንጫፍ

የዚህ ክፍል ሶስት አበይት ሀላፊነቶች የሚከተሉት ናቸው:

  • የመነሻ እና መንስኤ ምርመራዎች - በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የተከሰቱ ሁሉም የእሳት አደጋዎች መነሻቸውን እና መንስኤያቸውን የመመርመር ሃላፊነት፤ የእሳት መርማሪዎች ስራ ላይ ለሚገኙ ኩባንያዎች ከእሳት ደንብ ጥሰቶች እና ከእሳት ጉዳቶች ጋር በተያያዘ እገዛ ለማድረግ ከስራ ሰአት ውጪም ይመደቡላቸዋል።
  • የሰው ቤት አቃጣዮችን መመርመር - የሚመደቡት አባላት የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የእሳት ደህንነት ሕጎች የሚያስፈጽሙ ልዩ ፖሊሶች ይመደቡላቸዋል። ሆን ተብሎ በሰው የተጫሩ የእሳት አደጋዎች ናቸው የሚል ጥርጣሬ ሲኖር ምርመራዎች የማድረግ ሀላፊነት አላቸው። ቅርንጫፉ እሳት በተከሰተበት ቦታ ተቀጣጣይ ፈሳሾች እንዳይኖሩ የሚፈትሽባቸው ሁለት ፈጣን መፈተሻ መሳሪያዎችም አሉት።
  • የእሳት ጫሪ ህጻናት ኢንተርቨንሽን ፕሮግራም - ፕሮግራሙ የአጭር-ጊዜ ትምህርት ይሰጣል - ይህ የኢንተርቨንሽን ፕሮግራም ወላጆችን እና ህጻናትን ስለ እሳት ደህንነት እና እሳት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች የማስተማር አላማ ያለው ነው።.  ዕድሜአቸው ከ 2 እስከ 17 አመት ለሆናቸው ህጻናት የሚሰጥ ነው።  ሪፈራሎች በስራ ቀናት ወደ (202) 727-1600 መላክ አለባቸው። በድንገተኛ አደጋ ጊዜ፣ ወደ OUC በ (202) 373-3700 ይደውሉ፣ የእሳት ጫሪ ህጻናት እንተርቨንሽን ፕሮግራም አስተባባሪውን ይጠይቁ።

ከስራ ሰአታት ውጪ፣ የደንብ አስፈጻሚ ስታፎች በማይኖሩበት ጊዜ፣ ወደ OUC በ (202) 373-3700 ይደውሉ፣ እና ተረኛ ምድብተኛ የእሳት መርማሪ ይላክልዎታል።

እኛን የሚያገኙበት መንገድ

የእሳት ማርሻል ፅሕፈት-ቤት
1100 4th Street SW
Washington DC 20024
ስልክ: (202) 727-1614