Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

(አማርኛ) Frequently Asked Questions Right Care, Right Now - Amharic

ወደ 911 የሚደረጉ ጥሪዎች ሁሉ በፍጥነት ይመለሣሉ፥ ነገር ግን ሁሉም ጥሪዎች አንድ አይደሉም፡፡ ግባችን የ911 ደዋዮች ለሕክምና ፍላጎቶቻቸው ይበልጥ ተስማሚ ከሆነ የጤና አጠባበቅ ማዕከል ጋር ማገናኘት ነው፡፡ ይህም ምናልባት ወደ ሐኪም ቤት የድንገተኛ ክፍል ማጓጓዝን ሊያካትት ወይም ላያካትት ይችላል፡፡

የ Right Care, Right Now ፕሮግራም ግቦች የህሙማንን የጤንነት ሁኔታ እንዲሻሻል ማድረግ እና የዲሲ የእሳት እና ኢ/ኤም/ኤስ መምሪያ(FEMS) ሀብቶችን ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ጉዳትና ሕመም ላለባቸው ሕመምተኞች እንዲውል መጠበቅ ነው፡፡ ይህ በተጨናነቁ የሀኪም ቤቶች የድንገተኛ ክፍል ነፃ የሆኑ አልጋዎችን በጣም የታመሙ የድንገተኛ ታካሚዎች እንዲጠቀመባቸው ማዘጋጀትን ይጨምራል፡፡ መስተዳደሩ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት በላይ ከፍተኛ የሆነ የ EMS ጥሪዎች አሉበት፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አስቸኳይ ያልሆኑ የድንገተኛ ጥሪዎቻችን ለድንገተኛ ጊዜ ክፍል ውስጥ ያሉ ግብአቶቻችን ሁሉ ያሟጥጣሉ፡፡

የ Right Care, Right Now ፕሮግራም ከተጀመረ በኋላ 911 ላይ የሚደውሉ ድንገተኛ ያልሆኑ ጉዳቶች ወይም ህመሞች ታካሚዎች ወዲያውኑ በ 911 ማእከል ወይም በ FEMS የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪ ነርስ ይተላለፋሉ፡፡ ነርሷ ደዋዩን ጥያቄዎች በመጠየቅና የሕመሟን ወይም ሕመሙን ምልክቶች በማጤን ደዋዩን በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ ድንገተኛ ያልሆኑ ሕመሞች የህክምና መስጫ ማለትም የማህበረሰብ የህክምና ማዕከል ወይም ደዋዩ አቅራቢያ ወደ ሚገኝ ያስቸኳይ ጊዜ የሕክምና ጣቢያ ትልከዋለች፡፡ የሜዲኬይድእና የዲሲ የጤና እንክብካቤ አሊያንስ አባላት ወደ ህክምና ተቋሙ ሲሄዱና ሲመለሱ ነፃ መጓጓዣ ይሰጣቸዋል፡፡

ወደ 911 መቼ ልደውል?

ሕይወትዎን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለው ያሰቡት ወይም ሊጥል የሚችል ለምሳሌ የመተንፈስ ችግር፣ የደረት ሕመም፣ የልብ ሕመም፣ የደም ቧንቧ ህመም፣ እራስን መሳት፣ አደገኛ የሆነ አለርጂ፣ የአደጋ ወይም የመውደቅ ጉዳት ወይም ሌሎች፣ አደገኛ ወይም አስቸኳይ ሕመሞች ሲሆኑ ወደ 911 አስቸኳይ ለሆነ የድንገተኛ ሕክምና ሊደውሉ ይገባል(እራስዎት ወይም ሌላ ሰው)፡፡ ለአነስተኛ ሕመሞች ወይም አደጋዎች 911 ላይ መደወል የለቦትም፡፡ ለምሳሌ ለጉንፋን ወይም ለቫይረስ ለአነስተኛ መቆረጥ ወይም በመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና ባለሙያ ቀጠሮ በመያዝ ሊታከም ለሚችል ሕመም፡፡

911 ላይ ብደውል FEMS ሊመልስልኝና ወደ ሕክምና ማዕከል ሊያደርሰኝ ይችላል?

በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ ጉዳዮ አፋጣኝና ሕይወትዎን አደጋ ላይ የሚጥል ወይም ሊጥል የሚችል ድንገተኛ አደጋ ከሆነ 911 ማዕከል (የተዋሃዱ ግንኙነቶች ጽሕፈት ቤቶች) የሕመም ምልክቶችዎን የሚያጠኑ በቀጥታ ወደ ሐኪም ቤት የሚያደርሱዎትን ወይም የአሜሪካ የሕክምና ምላሽ(AMR)፣ የክፍሉ ሦስተኛ ወገን አገልግሎት ሰጪ ወደ ሐኪም ቤት ሊያጓጉዞት ይገባል የሚለውን የሚለዩትን የ FEMS የመጀመሪያ ደረጃ መላሾች ይልኩለታል፡፡

ጉዳዮ ድንገተኛ ሕመም ካልሆነ (1) ወደ Right Care, Right Now ሊዘዋወሩ የሚችሉ ሲሆን በስልክ መስመሩ ላይ የምትገኘውን ነርስ የሕመም ምልክቶችን በመስማት ተገቢ ሕክምና ሊያገኙበት ወደሚችሉበት የሕክምና ማዕከል ትመራዎታለች፡፡ ወይም (2) የ FEMS የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎች ሁኔታዎትን ይገመግምና በ FEMS ፕሮቶኮል እና የአሰራር ሂደት ብቁ ሆነው ከተገኙ በስልክ ከነርስ ጋር ያገናኝዎታል፣ ነርሷም የሕመም ምልክቶችን በመስማት ተገቢ ሕክምና ሊያገኙበት ወደሚችሉበት የሕክምና ማዕከል ትመራዎታለች፡፡

FEMS የስልክ ጥሪዬን ሊመልስልኝ እንደሚገባ ወይንም ወደ Right Care, Right Now መተላለፍ እንደሚገባኝ የ911

ወደየትኛው የሕክምና ክሊኒክ እንደምላክ የሚወሰነው እንዴት ነው?

ዋና የሕክምና አገልግሎት ሰጪ(ካለዎት)፣ ለመጨረሻ ጊዜ ሕክምና የተቀበሉበት ስፍራ፣ ያሉበትን ቦታ፡ ሰዓቱን፡ እንዲሁም የሕክምና አገልግሎት ሰጪዎችን መገኘትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነርሷ ተገቢ ከሆነው የሕክምና ሰጪ ጋር ታገናኝዎታለች፡፡

ነርሷ አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕክምና ክሊኒኩ የሕክምና ቀጠሮ ልታሲዝልኝ ትችላለች? ሰራተኞቹ መቼ እንደምደርስና ለምን እንደሆነ ያውቃሉ?

ለ Right Care, Right Now የስልክ መስመር ህመምተኞች እያንዳንዱ ክሊኒክ ድንገት መጥተው ለሚታከሙ ታካሚዎች ቀጠሮ ይሰጣል፡፡ ነርሷ እየሄዱበት ያለው ክሊኒክ በምን ሰዓት እንደሚደርሱና ምን አይነት ሕክምና እንደሚያስፈልጎት በመንገር መረጃ ትሰጣለች፡፡ በጤና ማዕከሉ እንደደረሱ በተቻለ ፍጥነት ወዲያውኑ ይታያሉ፡፡

በጉብኝቴ ወቅት የሕክምና ሰጪዎቹ መድኃኒት ያዝሉኛል?

አዎ የተመረጡት የሕክምና ሰጪዎች መድኃኒት ሊያዝሎት ይችላሉ፡፡

ከሕክምናክሊኒኮቹ በአንዱ የሕክምና ቀጠሮዬን ከተከታተልኩኝ በኋላ ወደ ቤት ስመለስ መጓጓዣ የሚሰጠኝ ከሆነ የታዘዙልኝን መድኃኒቶች በመንገድ ላይ መግዛት እችላለሁ?

የ ሜዲኬይድ ተጠቃሚ ወይም የዲሲ የጤና እንክብካቤ አሊያንስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ጤና ማዕከላቱ ያለዎትን ቀጠሮ ከጨረሱ በኋላ ወደ ቤትዎ የሚመልስዎት መጓጓዣ ይዘጋጅልዎታል፡፡

ከዚህ በፊት በታየሁበት ክሊኒክ ያለኝን የወደፊት ቀጠሮ ወይም ማንኛውንም ክትትል ለማድረግ 911 ላይ መደወል አለብኝ?

የለብዎትም፡፡ ማንኛውንም ለሕይወት አስጊ ያልሆኑ የሕክምና ቀጠሮዎች በቀጥታ ከዚህ በፊት ከታዩበት የሕክምና ማዕከል ጋር በመነጋገር ወይም አሁን ታማሚ ሆነው የተመዘገቡበት የሕክምና ማዕከል ካለ ወይም ሌላ ክሊኒኩ ወደላከዎት በማንኛውም የድንገተኛ አደጋ ያልሆኑ የሕክምና ማዕከላት ጋር ማድረግ ይችላሉ፡፡

በ Right Care, Right Now ያለችው ነርስ ያለሁበት ሁኔታ ወደ ሆስፒታሉ የድንገተኛ ክፍል የመጓጓዣ አገልግሎት እንደሚያስፈልገኝ ከወሰነች ምን ይከተላል?

በ Right Care, Right Now ያሉ ነርሶች በመሰረቱ መቀበል ያለባቸው ስልኮች በሆስፒታል በሚገኝ የድንገተኛ አደጋ ሕክምና ክፍሎች ሳይሆን የድንገተኛ አደጋ ባልሆነ ጤና እንክብካቤ በሚሰሩ የጤና ማዕከላት ሊታከሙ የሚችሉ ሕሙማንን ስልኮች ብቻ ነው፡፡ ይሁንና በ Right Care Right Now መስመር ላይ የምትገኘው ነርስ የእርስዎ ሁኔታ አስቸኳይ ወይም ድንገተኛ ስለሆነ በሐኪም ቤት ወይም በ FEMS የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎቹ ሊታዩ ይገባል ብላ ካሰበች የ FEMS የሕክምና ጓዶችን ወደ እርስዎ እንልካለን፡፡ የ FEMS የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎች ቀድመው በቦታው ደርሰው ከሆነ እና ነርሷ/ነርሱ ሆስፒታል ገብተው መታከም እንዳለብዎት ከወሰኑ፣ የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎቹ በ FEMS ወይም AMR አምቡላንስ ወደ ሆስፒታ እንዲጓጓዙ ያደርጋሉ።

ነርሶች የትምህርት ደረጃዎች ምንድ ናቸው?

ነርሶቹ በመስተዳደሩ ፍቃድ የሚሰጣቸው ሲሆን በድንገተኛ አደጋ ሕክምና ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ እንዲሁም ከአደጋ ጊዜ ሕክምና ጋር ይበልጥ ትውውቅ ያላቸው ናቸው፡፡

ከነርሷ ጋር ተነጋግሬ ካበቃሁ በኋላ አሁንም ወደ ሐኪም ቤት በአምቡላንስ መሄድ የምፈልግ ቢሆን ቀጥሎ የሚከሰተው ምንድን ነው?

የህመምዎን ምልክቶች በማጤን ነርሷ ለእርስዎ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ውሳኔዎን ታስተላልፋለች፡፡ የሚታይብዎት የሕመም ምልክቶች የድንገተኛ አደጋ ምልክቶች ካልሆነ ነርሷ ለእርስዎ የሚገባውን በከፍተኛ ሁኔታ ተስማሚ ወደሆነ የጤና ማዕከል ትልክዎታለች፡፡

ካለሁበት ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተካሄደውን ሂደትና የሕክምና ምርጫ ባልቀበለው ቅሬታዎቼን ማቅረብ የምችለው በምን አይነት መልኩ ነው?

ወደ FEMS በ 202-673-3320 ላይ በመደወል ቅሬታዎችን ማቅረብ ይችላሉ፡፡