Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Special Events Office of the DC Fire and EMS Department - Amharic

Apply online
የኮሎምቢያ ዲስትሪክት በየአመቱ ከአምስት መቶ በላይ ልዩ ህዝባዊ ዝግጅቶችን ታስተናግዳለች።  ልዩ ዝግጅት ማለት እንደ ፈስቲቫል፣ የጎዳና ላይ ውድድሮች፣ የሰልፍ ትእይንት፣ የፊልም ቀረጻዎች፣ ማራቶን፣ ለአላማ የሚደረግ ህዝባዊ የእግር ጉዞ ወዘተ የመሳሰሉ በግል ወይንም በመንግስት ቦታ የሚካሄዱ ክንዋኔዎችን ያጠቃለለ ነው። እነዚህ ዝግጅቶች አዝናኝ ወይንም አስደማሚ ተግባራት፣ የምግብ እና የመጠጥ አቅርቦቶች የሚደረጉባቸው እና የተለያዩ የከተማዋ ድርጅቶች ትብብር የሚጠይቁ ሊሆኑ ይችላሉ። የዝግጅትዎ ደህንነት ሁኔታ የመገምገም እና ለህዝቡ ደህንነት በሚበጅ መንገድ መመሪያ መስጠት የልዩ ዝግጅቶች ጽሕፈት-ቤት አብይ ሀላፊነት ነው።  በተጨማሪም፣ ልዩ ዝግጅቶች በማስመልከት የሚጠየቁ አገልግሎቶችም በተቋማችን ሊሳለጡ ይችላሉ።
 
የአገልግሎት ጥያቄ በሚከተሉት እና ሌሎች አቀራረቦች ሊቀርብ ይችላል:
  • የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች አገልግሎት
  • እሳት ማጥፊያዎች
  • የብዙሃን ጉዳቶች
  • እዝ እና ቁጥጥር
  • የእሳት እና የህይወት ደህንነት
  • የውሃ ደህንነት እና ከአደጋ ማትረፍ
ሁሉንም የአገልግሎት ጥያቄዎች ማጽደቅ የሚቻለው ከዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች መምሪያ በሚያመቷቸው የይሁኝታ ማረጋገጫዎች ላይ በመመስረት ነው። ለዝግጅትዎ የአገልግሎት ጥያቄ የሚከተለውን ሊንክ በመጠቀም ማቅረብ ይቻላል።
የልዩ ዝግጅቶች በማስመልከት የሚቀርቡ የአገልግሎት ጥያቄዎች ከማናቸውም አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ኦንላይን ማስረከብ ይቻላል። እባክዎ የሚከተለውን የአስፈላጊ ሰነዶች ዝርዝር ይገምግሙ እና የልዩ ዝግጅት አገልግሎት ጥያቄ ከማቅረብዎ በፊት እነዚህን ሰነዶች መኖራቸውን ያረጋግጡ።  የአገልግሎት ጥያቄዎ ከደረሰን በኋላ፣ የልዩ ዝግጅቶች ጽሕፈት-ቤታችን ተወካይ በኢሜይል ወይንም በስልክ ያነጋግርዎታል ከዛ በጥያቄዎ ሂደት ዋናው ከእርስዎ ጋር የሚገናኝ ሰው ሆኖ ይሰራል።  ሁሉም ሰነዶች እና ገቢ የሚሆኑትን (አስፈላጊ ከሆን) ተፈርሞባቸው የግድ ዝግጅትቱ ከመከናወኑ ከሰላሳ (30) ቀናቶች በፊት ለልዩ ዝግጅቶች ጽሕፈት-ቤት ማስረከብ ያስፈልጋል። እባክዎ ለአገልግሎት ጥያቄዎ ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ መረጃዎችዎ በተቻለ መጠን በዝርዝር ያቅርቡ።
 
ስረዛዎችን በጽሑፍ ለሚከተለው አካል ማሳወቅ ያስፈልጋል:
Special Events 
Homeland Security and Special Operations 
DC Fire and EMS Department
1338 Park Road NW
Washington, DC 20010 
ስልክ: (202) 673-6614
 
ማንኛውም ዝግጅት ተጨማሪ ፈቃዶች፣ ተቀባይነቶች፣ ወይንም አገልግሎቶች ከከተማው መንግስት ተቋማት ማግኘት አለባቸው። የሚከተለው ዝርዝር አካታች ነው ይሁን እንጂ; ለልዩ ዝግጅቶች ተጨማሪ ግምገማዎች፣ የፈቃዶች እና የአገልግሎት መስፈርቶች ብቻ የተወሰነ አይደለም:
የሆምላንድ ደህንነት ልዩ ክንዋኔዎች
አድራሻ:1338 Park Road NW | 20010
ዋርድ: 1
ስልክ: (202) 673-6614
ኢሜይል: [email protected] 
ኢሜይል: [email protected]
 
የክፍያ መረጃ:
ለባንክ መላኪያ ዝርዝሮች ወደ ሎሬታ ዎከር ይደውሉ
ሁሉም ቼኮች ወደሚከተለው አድራሻ በፖስታ ይላኩ:
Loretta A. Walker, CPA
Cluster Controller
Public Safety & Justice Cluster
300 Indiana Avenue, NW
Suite 4068
Washington, DC 20001
ስልክ ቁጥር (202) 727-4317
ፋክስ  (202) 724-7518