Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Juvenile Firesetter's Intervention Program - Amharic

Match on fire

እውነታዎች

  • እሳቶች እና ቃጠሎዎች ቀዳሚ የህጻናት ጉዳት እና ሞት መንስኤዎች ናቸው።
  • የህጻናት በእሳት መሞት ከአዋቂዎች ጋር ሲወዳደር በእጥፍ ይበልጣል።
  • የሚድሁ ህጻናት ሳይቀሩ በክብሪት ወይንም በመለኮሻ እሳት ሊጭሩ ይችላሉ።
  • ልጆች በጫሩዋቸው የእሳት አደጋዎች ከሚሞቱ 100 ሰዎች ውስጥ 85 ህጻናት ናቸው።
  • እሳት ጫሪ ማለት በማወቅ ይሁን ባለማወቅ እሳት የሚጭሩ ዕድሜያቸው ከ 18 አመት በታች የሆኑ ልጆች ናቸው።

ፕሮግራሙ

የህጻናት እሳት ጫሪዎች ኢንተርቬንሽን ፕሮግራም ፕሮግራም እሳት የመጫር ባህሪ ያላቸው ዕድሜያቸው ከ 2-17 አመት የሆኑ ህጻናት የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ የሚሰጥ የአራት ሳምንት ኢንተርቬንሽን ፕሮግራም ነው። የፕሮግራሙ አላማ ወላጆች እና ህጻናት ስለ እሳት ደህንነት እና እሳት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ ነው። ይህ ፕሮግራም የህጻናት የትምህርት አገልግሎቶች የማግኘት ፍላት ከመገምገም በተጨማሪ፣ እሳት ባይጭሩም እሳት የመጫር ፍላጎት ያላቸው ህጻናትንም ያስተምራል።

ሪፈራሎች/ ጥቆማዎች

በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሪፈራሎች/ ጥቆማዎች በእሳት አደጋ ዲፓርትመንት ሰራተኞች እና የእሳት አደጋ ፍጻሜ ላይ ከተሳተፉ ህጻናት ጋር ግንኙነት ባደረገ የህጻናት ፍርድ-ቤት የሚደረጉ ሲሆን; ይሁን እንጂ፣ ማንኛውም የህጻናቶች ደህንነት የሚያሳስበው ሰው (ወላጆች፣ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ ጎረቤቶች፣ ወይንም ሌሎች) ደውለው እርዳታ ሊጠይቁ ወይንም ከታች ወዳለው አገናኝ በመግባት የሪፈራል/የጥቆማ ቅጽ ሊሞሉ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ያናግሩ/ ያግኙ:
የህጻናት እሳት ጫሪዎች ኢንተርቬንሽን ፕሮግራም ፕሮግራም
(202) 727-2215 ወይንም (202) 727-1600

የሪፈራል ቅጽ
ከ TTY ጋር ይገናኙ: 
711