Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

FEMS Fire Safety Education - Amharic

እንኳን ወደ የዲስትሪክት ኮሎምቢያ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት- የእሳት ደህንነት ትምህርት ገጽ በደህና መጡ። ጉብኝትዎ ጠቃሚ ሆኖ እንደሚያገኙት እና ከጉብኝትዎ ሲመለሱ የተሸለ የእሳት ደህንነት እውቀት ይዘው እንደሚሄዱ እናምናለን!  እንደ ወላጅ፣ የቤትዎ ደህንነት የበለጠ የሚያረጋግጡበት ወሳኝ መረጃ ያገኛሉ። እንደ አስተማሪ፣ የእሳት ደህንነትን የሚያስተምሩበት አስፈላጊ ማቴርያል የሚያዘጋጁበትን መንገድ ያገኛሉ። ተማሪ ከሆኑ ደግሞ፣ የእሳት ደህንነት ለማስተማር የሚረዱ ሁሉም አይነት የመዝናኛ ጌሞች እና እንቅስቃሴዎች ያገኛሉ። 

 

DCFEMS Fire Safety Education

 

ለወላጆች
በእያንዳንዱ የትምህርት አመት፣ የዲስትሪክት ኮሎምቢያ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት ህጻናትን ስለ እሳት አደገኝነት፣ እና እቤትዎ ውስጥ እሳት ከተነሳ ምን ማድረግ እንዳባቸው በማስመልከት የማስተማር ድርሻን ይወጣል። ይሁን እና ምንም እንኳ ልጅዎ ብዙ ትምህርት ቢማር፣ እቤታቸውን ከእርስዎ እገዛ ውጪ ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ አይችሉም። እርስዎ ብቻ ነዎት ይህንን ማድረግ የሚችሉት። የቤትዎ ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ጥቂት ደቂቃዎች መመደብ ይችላሉ?

እባክዎ ከታች ያለው የመፈተሸ ዝርዝር ይመልከቱ:
የቤት እሳት ደህንነት መፈተሸ ዝርዝር
 
ለአስተማሪዎች 
እንደ አስተማሪ፣ ጊዜዎ ውድ መሆኑን እናውቃለን። በተጨማሪ እርስዎ ተማሪዎችዎን ከእሳት ደህንነት ጋር በተያያዘ በቻሉት መጠን በጣም ጥሩ ትምህርት ለማስተማር እንደሚተጉ ይገባናል። ይህ ጥረት ከማገዝ አንጻር፣ የዲስትሪክት ኮሎምቢያ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት እንደ ጌሞች፣ እንቅስቃሴዎች እና መረጃዎች የመሳሰሉ ማስተማሪያ ክፍል ውስጣ ማስተማርን የሚያጠናክሩ በጣም ጠቃሚ ማቴርያሎችን ለማቅረብ ይተጋል።
 
ለህጻናት!
በአንድ ነገር ላይ ጥሩ ብቃት እንዲኖርዎ፣ መለማመድ ይኖርብዎታል። ጥሩ፣ አይጨነቁ። የእሳት ደህንነት ልምምድ ማድረግ እጅግ በጣም አዝናኝ ሆኖ አያውቅም። ከታች ያለው አገናኝ ይፈትሹ እና የከለር ገጾች፣ እንቅስቃሴዎች፣ እና እሳት አደጋን የሚመለከቱ ጌሞች ሳይቀር ያገኛሉ።
 
የማቴርያሎች አገናኞች: