Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Ambulance Billing Questions - Amharic

የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት አምቡላንስ (Fire and Emergency Medical Services Department) ስለተጠቀሙ እናመሰግኖታለን። ህክምና ባደረጉልዎ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞቻችን እና ከ 2,000 በላይ  ዩዲሲ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ፈንታ፣ እባክዎ እርስዎ ከበሽታዎ ወይንም ከጉዳትዎ በፍጥነት እንዲያገግሙ ያለንን ምኞች ይቀበሉን። ዲፓርትመንታችን ስለ ደንበኞች አገልግሎት፣ የአምቡላንስ ክፍያ፣ የመድህን ክፍያዎች፣ የችግር ጊዜ እርዳታ እና ሌሎች ከድንገተኛ አደጋ አገልግሎቶች ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች በተመለከተ ለሚቀርቡሎት ጥያቄዎች ይሄንን ድረ-ገጽ በመጠቀም ምላሽ ይሰጣል። የተለመዱ ጥያቄዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ።


ዲስትሪክቱ ለምንድነው የአምቡላንስ ክፍያ የሚጠይቀው?

የዲሲ ነዋሪዎች የሚያገኙዋቸው የድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች (EMS) የግብር ወጪ ለመቀነስ። የእሳት እና የ የድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንቱ የአምቡላንስ ክፍያ ሲያስከፍል ከሰላሳ አመታት በላይ  ሆኖታል። የዲስትሪክቱ አስተዳደር ለእነዚህ ክፍያዎች ፈቃድ ሲሰጥ የድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ለነዋሪዎች እና ለገብኚዎች የማቅረብ የግብር ወጪ ለማጣጣት ነው። አብዛኛው የስራ ማስኬጃ ወጪ ከግብር በሚሰበሰብ ገቢ ሲሸፈን፣ ከመድህን ኩባንያዎች የሚሰበሰቡ የአምቡላንስ ክፍያዎች የድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ላይ ወጪ ከሚደረገው እያንዳንዱ $8 ላይ $1 ገደማ ይሸፍናል። ይህ ብዙ ባይመስልም፣  የተገኘ ገንዘብ ከአምቡላንስ ክፍያዎች የሚሰበሰብ ገቢ ባይኖር ኖሮ፣ የድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ለማገዝ ሲባል ገንዘብ ከሌሎች የዲስትሪክቱ ፕሮግራሞች እንዲዛወር ይደረግ ነበር። በተጨማሪ፣ ከ 15% በላይ የሚሆኑት ዲስትሪክቱ ላይ የድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች የሚጠቀሙ ታካሚዎች የቨርጂንያ ወይንም ሜሪላንድ ነዋሪዎች ናቸው። የገንዘብ ምንጫችን ግብር ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ የቨርጂንያ እና ሜሪላንድ ነዋሪዎች የ "ነጻ፣" ስርአት መጠቀም ሲኖርባቸው የዲሲ ነዋሪዎች ደግሞ ክፍያውን መክፈል ይጠበቅባቸው ነበር።
 

የሚከፈሉት ክፍያዎች ምን አይነትና በአምቡላንስ ለመሄድስ ስንት ያስከፍላል?

የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምናዲፓርትመንት በ 67ኛው እትም፣ ቁጥር 39 የፌደራል ሬጂስተር ላይ በተገለጸው መሰረት የአምቡላንስ አገልግሎቶች ነጻ የክፍያ የግዜ ሰሌዳ በተመለከተ "የMedicare እና Medicaid አገልግሎቶች ማእከላት (CMS)" ነው የሚከተለው። አዳዲሶቹ ክፍያዎች ከጥር 1, 2009 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • BLS መጓጓዣ: የ "መሰረታዊ የህይወት እገዛ" (BLS) የእንክብካቤ ደረጃ የሚሰጣቸው ታካሚዎች $428 ይከፍላሉ። BLS ዝቅተኛ ወይንም መሰረታዊ ሕክምና እና የወሳኝ ምልክቶች ቁጥጥርን ያካትታል። አልፎአልፎ፣ ኦክስጅን መስጠትንም ሊያካትት ይችላል። የ BLS (መሰረታዊ የህይወት እገዛ) መጓጓዣ ለማግኘት የሚቀርቡ ምክንያቶች ሁልጊዜም "ህይወትን አደጋ ላይ የማይጥሉ መሆን ይኖርባቸዋል።"
  • ALS መጓጓዣ: "የከፍተኛ የህይወት እገዛ" (ALS) ደረጃ ሕክምና የሚሰጣቸው ታካሚዎች $508 ይከፍላሉ።
  • ALS-2 (የከፍተኛ የህይወት እገዛ) ማጓጓዣ: የተራዘመ "ከፍተኛ የህይወት እገዛ " (ALS) ደረጃ ሕክምና የሚያገኙ ታካሚዎች $735 ይከፍላሉ። ALS-2 (የከፍተኛ የህይወት እገዛ) ማናቸውም ከላይ የጠዘረዘሩት የ ALS ሕክምናዎች፣ ማስተንፈሻ ትቦ መሰካትን ጨምሮ፣ CPR፣ ብዙ መድሀኒቶች ወይንም ሌላ የተራዘመ ሕክምና ያካትታል።የ ALS-2 (የከፍተኛ የህይወት እገዛ) ማጓጓዣ ለማግኘት የሚቀርቡ ምክንያቶች ሁልጊዜም "ወድያውኑ ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ መሆን አለባቸው።" የጉዞ ርቀት: ሁሉም በአምቡላንስ የሚጓዙ ታካሚዎች በአንድ
  • ማይል $6.55 ይከፍላሉ። የጉዞው ርቀት አደጋው ከተከሰተበት ቦታ እስከ ተቀባዩ ሆስፒታል ነው የሚለካው። ከላይ የተገለጹት ክፍያዎች እንደሁኔታው ሊለዋወጡ ይችላሉ።

    የመጨረሻው የዲስትሪክት ኮሎምቢያ የአምቡላንስ ክፍያ የሚገልጽ ማስታወቂያ የዲፓርትመንቱ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል ወይንም በጥያቄዎ መሰረት በፖስታ ሊላክልዎ ይችላል። ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ በስልክ ቁጥር (202) 673-3331 ወደ ደንበኞች አገልግሎት ማእከላችን ይደውሉ። የእሳት አደጋ መከላከያ ተሸከርካሪ ከአምቡላንሱ ጋር አብሮ ይመጣል።

ለሱም እከፍላለሁ? አይ፣ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና ዲፓርትመንት የአምቡላንስ ጉዞ ክፍያ ብቻ ነው የሚያስከፍለው። የእሳት አደጋ መከላከያ መኪኖች በ 911 ሲደወልላቸው ከአምቡላንሱ የፈጠነ ምላሽ ይሰጣሉ፣ ስለሆነም የአደጋ መከላከያ ሰራተኞች ከማንም በፊት ፈጥነው ይደርስልዎታል።
ለዚህ አገልግሎት ምንም ክፍያ መክፈል አይጠበቅብዎትም። ምርመራ የተደረገልዎ እና/ወይንም ህክምና የተደረገልዎ ቢሆንም ወደ ሆስፒታል በአምቡላንስ ለመጓዝ የማይፈልጉ ከሆነ ምንም ክፍያ አይከፍሉም።

የአምቡላንሱ ሰራተኞች ለምንድነው የግሌን መረጃ እንድሰጣቸው የሚጠይቁኝ?

ማንነትዎን ለማረጋገጥ እና ማጭበርበርን ለመከላከል ነው። የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምናዲፓርትመንት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ክፍያ ስለሚጠይቅ፣ የአምቡላንሱ ሰራተኞች ስም፣ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር፣ የትውልድ ቀን፣ የቤት አድራሻ እና የስልክ ቁጥር በመጠየቅ የታካሚውን ማንነት እንዲያጣሩ ይታዘዛሉ። እንደ ሁኔታው፣ የጤና መድህን፣ የቤትመኪና መድህን ወይንም የስራ ሁኔታ መረጃም ሊጠይቁ ይችላሉ።
ዲፓርትመንታችን ታካሚዎችን ከማጭበርበር ለመታደግ እና፣ ከተቻለ ደግሞ፣ እርስዎ የጤና እንክብካቤ ወይንም ሌላ መድህን ሽፋን ያለዎት እንደሆነ ለማረጋገጥ የማንነት ማጣራት ስራ ይሰራል።

የጤና መድህን ሽፋኔ የአምቡላንስ ክፍያ ይከፍልልኛል? አብዛኛው ጊዜ፣ አዎ። የ MediCAID፣ Alliance ወይንም የ MediCARE ፕሮግራሞች ሽፋን ያላቸው የዲስትሪክት ኮሎምቢያ ነዋሪዎች ለአምቡላንስ ከኪሳቸው የሚከፍሉት ክፍያ አይኖራቸውም። የግል የጤና እንክብካቤ መድህን ሽፋን ያላቸው የዲሲ ነዋሪዎች ደግሞ ከ $100 የሚያንስ የድርሻ ክፍያ ወይንም ተቀናሽ ክፍያ እንዲከፍሉ ሊጠየቁ ይችላሉ።
የ MediCAID፣ MediCARE ወይንም የሌላ የፌዴራል ፕሮግራሞች ሽፋን የሌላቸው የዲሲ ነዋሪዎች ያልሆኑ አምቡላንስ ተጠቃሚዎች፣ መክፈል የሚጠበቅባቸው ሙሉ የአምቡላንስ ክፍያዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው።

መጠየቂያ ቅጾች ሞልተው እንዲያስረክቡ ወይንም ሌላ መረጃ እንዲያቀርቡ ሊጠየቁ ይችላሉ። የጤና እንክብካቤ መድህን ባይኖረኝስ? እኛ ልንረዳዎት እንችላለን! የጤና እንክብካቤ መድህን የሌሎት የዲሲ ነዋሪ ከሆኑ፣ ለ MediCAID ብቁ ካልሆኑ፣ እባክዎ በ (888) 828-8019 ይደውሉ እና ከደንበኛ አገልግሎት ስፔሻሊስት ጋር ለመነጋገር ይጠይቁ። የክፍያ ፅሕፈት-ቤት ሰራተኞቻችን የገቢ ብቁነት መስፈርቶች ለሚያሟሉ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች ነጻ የጤና እንክብካቤ አቅራቢ የዲሲ ጤና ፕሮግራም ዲፓርትመንት የሆነው DC HealthCare Alliance አድራሻ እና የመጠየቂያ መረጃ ይሰጠዎታል።

ለአረጋውያን ዜጎች የሚመለከቱ ፕሮግራሞች ይኖራሉ?

አዎ! ከጥር 1, 2009 ጀምሮ፣ እርስዎ የ MediCARE ሽፋን ያለዎት የዲሲ ነዋሪ ከሆኑ፣ በ MediCARE ወይንም በሌላ የመድህን እቅድ ሽፋን የማያገኙ የአምቡላንስ ክፍያዎች መክፈል አይጠበቅቦትም። እባክዎ በአምቡላንሱ ሰራተኞች የተሰጠዎ ወይንም በአምቡላንስ ክፍያ ፅሕፈት-ቤታችን አማካኝነት በፖስታ የተላከልዎ ማናቸውም የ MediCARE ማረጋገጫ ቅጾች መፈረምዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
እኔ የዲሲ ነዋሪ አይደለሁም የጤና መድህንም የለኝም።

የአምቡላንስ ክፍያ መፈጸሚያ የፖስታ አድራሻ እና የአድራሻ መረጃ የቱ ነው?

እባክዎ ክፍያዎች፣ ቅጾች፣ ደብዳቤዎች እና ሌሎችም ጨምሮ ሁሉንም የአምቡላንስ ክፍያን የሚመለከቱ ሰነዶችን በፖስታ ወደ ሚከተለው ይላኩ:

DC Fire and EMS Department
P.O. Box 27767
Washington, DC 20038

 

ቼኮች ለሚከተለው ተከፋይ እንዲሆኑ አድርግ:

የዲስትሪክት ኮሎምቢያ ግምጃቤት
ዋናው ስልክ: 1(888) 828-8019

ደህንነቱ የተጠበቀ የድረገጽ ጥያቄ: www.emsclaims.net
እባክዎ የከተማ/የሀገር ስም ይምረጡ" ከሚለው ላይ "የዲስትሪክት ኮሎምቢያ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና"ይምረጡ  

የህክምና መዛግብቶች መረጃ:(202) 673-2039

HIPAA/PRIVACY/FOIA መረጃ: (202) 673-3397

HIPAA እና ግላዊነት። የዲስትሪክት ኮሎምቢያ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምናዲፓርትመንት የአምቡላንስ ክፍያዎች መከፈላቸው ለማረጋገጥ ጥበቃ ስር የሚገኘው የጤና መረጃዎ (PHI) ሊጠቀም ይችላል። ይህ የመድህን ክፍያ ጥያቄዎችን ማስረከብ፣ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ ላለባቸው ሌሎች ሶስኛ ወገኖች የክፍያ ጥያቄ ማቅረብ፣ ወይንም ክፍያ መጠየቂያ ወደ እርስዎ በፖስታ መላክን ያካትታል።

የክፍያ ጥያቄዎች በቀጥታ ወይንም በሶስተኛ ወገን የክፍያ ኩባንያ እና/ወይንም ክፍያ ሰብሳቢ አካል አማካኝነት ሊቀርቡ ይችላሉ። PHI ለክፍያ ክትትል አላማ መጠቀም ለቀረቡት አገልግሎቶች የተከፈለ ክፍያ አያያዝ፣ የህክምና ወሳኝነት ውሳኔዎች እና ግምገማዎች እንዲሁም ያልተከፈሉ ክፍያዎችን መሰብሰብ ሊያጠቃልል ይችላል። የኮንትራት ውል የገቡ ሰራተኞችን ጨምሮ የተመደበው ኤጄንሲ ሰራተኞች "ችግር" ምደባ፣ የህክምና እርዳታ ፕሮግራሞች ወይንም ሌሎች ልዩ እገዛዎችን ጨምሮ ለተወሰኑ አገልግሎቶች ብቁ ስመሆንዎ ለመገምገም PHI አጠቃቀምዎን ሊገመግሙ ይችላሉ።

 

ከ TTY ጋር ይገናኙ: 711
 

 

Contact TTY: 
711