Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

CPR Training Program - Amharic

የ CPR የስልጠና ፕሮግራም EMTs የልምምድ CPR

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች (DC Fire/EMS) ዲፓርትመንት በአሜሪካ የልብ ማህበር መመሪያዎች የተመሰረተ የልብ እና የሳንባ ማገገሚያ (Cardio-Pulmonary Resuscitation, CPR) ስልጠና ይሰጣል።

የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ቤወሩ የመጀመሪያው እና ሶስተኛው ሰኞ ላይ ለማህበረሰቡ አባላቶች ስልጠና ይሰጣሉ።  የልብ አዳኞች/CPR/AED/1ኛ የሕክምና እርዳታ ስልጠና ደግሞ በየወሩ የመጀመሪያው እና ሶስተኛው ሀሙስ ላይ ለማህበረሰቡ አባላት ይሰጣል።

የኦንላይን CPR ችሎታዎች በቀጠሮ ብቻ ማግኘት ይቻላል። ትምህርቶቹ ተማሪዎች የአዋቂዎች፣ የህጻናት እና የጨቅላዎች CPR ሰርትፊኬሽን እንዲያገኙ ያደርጋሉ። ስልጠና ኮርሶቹን በስኬት ካጠናቀቁ በኋላ፣ ተሳታፊዎች ለሁለት አመት የሚያገለግል ወረቀት ምስክር ይሰጣቸዋል።

የምንቀበላቸው ሰልጣኞች ቁጥር ውሱን ስለሆነ አስቀድመው መመዝገብ ይኖርብዎታል። ከነዚህ ስልጠናዎች ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ክፍያዎች አሉ። 

ልብ አዳኞች CPR/AED - $40; ይህ ኮርስ መማሪያ ክፍል ውስጥ የሚሰጥ፣ በቪድዮ እና በአስተማሪ የታገዘ የአዋቂዎች CPR እና የ AED አጠቃቀም እንዲሁም አዋቂዎች መዘረርን እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል የሚያስተምር ነው።

ልብ አዳኝ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ - $45; ይህ ኮርስ መማሪያ ክፍል ውስጥ የሚሰጥ፣ በቪድዮ እና በአስተማሪ የታገዘ ተማሪዎችን የአደጋ ጊዜ ሕክምና አገልግሎት ሰጪዎች (EMS) በአደጋ ቦታው እስኪደርሱ ድረስ ድንገተኛ አደጋ ከደረሰ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ደቂቃዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚማሩበት ነው።

ልብ አዳኝ CPR/AED/የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ - $70; ይህ ኮርስ የ CPR/AED እና የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ አጠቃሎ የያዘ ነው።

ልብ አዳኝ የሕፃናት የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ (ስፔሻሊቲ) - $45; ይህ ኮርስ የህጻናት ህክምና አቅራቢዎችን እና ሌሎችን የህጻናት በሽታ እና ጉዳት እንዴት መያዝ እና ምላሽ መስጠት እንዳባቸው ያስተምራቸዋል።

የጤና እንክብካቤ አቅራቢ (CPR ሰርትፊኬሽን) - $65; ይህ ኮርስ ብዙ የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎችን ብዙ ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድንገተኛ አደጋዎችን የሚለዩበት፣ CPR የሚሰጡበት፣ AED የሚጠቀሙበት፣ እና መዘረርን ደህንነቱ በተጠበቀ፣ በተገቢው ጊዜ እና በተሳካ ሁኔታ የሚያስተካክሉበት ብቃት እንዲኖራቸው ለማስቻል የተዘጋጀ ነው።

የጤና እንክብካቤ አቅራቢ (CPR ሰርትፊኬሺን) - $50

ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ከ CPR ስልጠና ዲፓርትመንት ጋር በስልክ ቁጥር (202) 673-6901 ይገናኙ።
ትምህር የሚሰጥበት ቦታ 4600 Livingston Road, SE. #3 ፎቅ, Washington, DC 20032።  

እጆችን ብቻ CPR/AED - በነጻ

እነዚህ ትምህርቶች የእጆችን ብቻ CPR እና AED ግንዛቤ የሚፈጠርባቸው ናቸው። ስልጠናው ተሳታፊዎችን የእጅ አቀማመጣቸው ላይ፣ የማሳረፍ ፍጥነትዎ እና በየሁለት ደቂቃው ልዩነት ስንት ግዜ መግፋት እንዳብዎ ይማሩበታል።  ለተጨማሪ መረጃ ወደ ወደ እጆች በልቦጅ ላይ CPR ፕሮግራም ገጽ ይሂዱ።
ከ TTY ጋር ይገናኙ: 711

ተዛማጅ ይዘት: 
እጆች በልቦች ላይ CPR ፕሮግራም