Special Events Office of the DC Fire and EMS Department - Amharic
የኮሎምቢያ ዲስትሪክት በየአመቱ ከአምስት መቶ በላይ ልዩ ህዝባዊ ዝግጅቶችን ታስተናግዳለች። ልዩ ዝግጅት ማለት እንደ ፈስቲቫል፣ የጎዳና ላይ ውድድሮች፣ የሰልፍ ትእይንት፣ የፊልም ቀረጻዎች፣ ማራቶን፣ ለአላማ የሚደረግ ህዝባዊ የእግር ጉዞ ወዘተ የመሳሰሉ በግል ወይንም በመንግስት ቦታ የሚካሄዱ ክንዋኔዎችን ያጠቃለለ ነው። እነዚህ ዝግጅቶች አዝናኝ ወይንም አስደማሚ ተግባራት፣ የምግብ እና የመጠጥ አቅርቦቶች የሚደረጉባቸው እና የተለያዩ የከተማዋ ድርጅቶች ትብብር የሚጠይቁ ሊሆኑ ይችላሉ። የዝግጅትዎ ደህንነት ሁኔታ የመገምገም እና ለህዝቡ ደህንነት በሚበጅ መንገድ መመሪያ መስጠት የልዩ ዝግጅቶች ጽሕፈት-ቤት አብይ ሀላፊነት ነው። በተጨማሪም፣ ልዩ ዝግጅቶች በማስመልከት የሚጠየቁ አገልግሎቶችም በተቋማችን ሊሳለጡ ይችላሉ።
የአገልግሎት ጥያቄ በሚከተሉት እና ሌሎች አቀራረቦች ሊቀርብ ይችላል:











