Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Operational Permits - Amharic

የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ክፍል የእሳት መከላከል ክፍል ጉዳት ሊያስከትሉ በሚችሉ እና የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ህብረተሰብ፣ ለደንበኞች እና ጎብኚዎች ደህንነት አስጊ በሆኑ የንግድ ስራዎች ላይ የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች፣ ኩባንያዎች እና የንግድ ድርጅቶች ስራዎቻቸው ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እያካሄዱ መሆናቸውን የመቆጣጠር ሀላፊነት አለው።

ይህንን እዉን ለማድረግ፣ የእሳት ደንብ በሚገባ መከበሩ ለማረጋገጥ ግምገማ ሊደረግባቸው የሚገቡ እና ተገቢ ማጣራት ከተደረገ በኋላ ከእሳት ሀላፊው የስራ ፈቃድ ሊሰጣቸው የሚገባ የተለዩ የስራ ክንዋኔ እና አሰራሮች አሉ።

የስራ ፈቃዶች በእሳት ደንብ ማጠናከሪያ የ IFC (2008) እትም እና 12 DCMR 12H በሚለው አርእስት ላይ በግልጽ በተቀመጠው ሕግ መሰረት ሊሰጡ ይገባል። Operational permits are required as specified in the IFC 2006 Edition and the Title 12 DCMR 12H Fire Code Supplement (2008).

የስራ ፈቃዱ የእሳት መከላከል ክፍሉን የአደገኛ አጠቃቀም ወይንም ማከማቻ የመፈተሸ ዕድል በመስጠት፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ እና ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ስጋቶችን ለይቶ በማወቅ፣ ሁሉም በስራ ጊዜ ሊከሰቱ የየሚችሉ የእሳት እና የህይወት ደህንነት ችግሮች መፍትሄ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል።

የስራ ፈቃዶች የሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ከዲሲ የእሳት እና የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት የእሳት መከላከል ክፍል ማግኘት ይችላሉ፤ አድራሻ 1100 4th Street SW Suite E700, Washington, DC  20024, ስልክ (202) 727-1614። የ FPD ክፍል የስራ ሰአታት ከ 8:15 AM እስከ 16:45 PM፣ ከሰኞ እስከ አርብ።

ብናኝ የሚፈጥሩ ምርቶች፣ ካርኒቫሎች እና ትርኢቶች፣ አውደርእዮች እና የንግድ ትርኢቶች፣ ኢንዳስትሪያላዊ ምድጃዎች እና የተረፈምርት አያያዞች ጨምሮ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ብዙ ሁኔታዎች የስራ ፈቃድ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

እባክዎ የተሟላ ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ይምረጡ።  Please select here for the complete list.

Contact TTY: 
711