እኛን ለማግኘት
የእሳት ማርሻል ጽህፈት-ቤት
1100 4th Street SW
Washington DC 20024
ስልክ: (202) 727-1614
የፍተሻ አገልግሎት ጥያቄ
ድርጅቶች የእሳት ደንብ ተከትለው እየሰሩ መሆናቸው ለማረጋገጥ የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች መምሪያ የእሳት መከላከል ክፍል በየአመቱ በሺዎች በሚቆጠሩ ድርጅቶች ላይ ፍተሻ ያደርጋል። በዲስትሪክቱ መንግስት ፈቃድ የመስጠት ስልጣን የተሰጠው ተቋም የንግድ ድርጅቶቹ የቢዝነስ/ የስራ ፈቃድ እድሳት እንዲያደርግላቸው እነዚህን ፍተሻዎች ማስደረግ እንዳለባቸው ግዴታ ይጥልባቸዋል።
የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ፈቃድ በማደስ ሂደት የሚጫወተው ወሳኝ ሚና የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የእሳት ፍተሻ እንዲያደርግላቸው እንዴት መጠየቅ እንዳለባቸው በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የንግድ ድርጅት ለሚያንቀሳቅሱ ሰዎች ማሳወቅ የዚህ ገጽ አላማ ነው።
በዚህ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ላይ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች የተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
ምርቶች እና እቃዎች ከሚሸጡ የችርቻሮ/ የሸቀጦች ንግድ ድርጅቶች አንስቶ ለህጻናት እና ለአረጋውያን እንክብካቤ እስከሚሰጡ የመዋያ ተቋማት፣ ሁሉም ኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የንግድ ድርጅቶች ፈቃዳቸው በሚያሳድሱበት ጊዜ የእሳት ፍተሻ ማስደረግ ይኖርባቸዋል።
የንግድ ድርጅት ባለቤቶች የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የእሳት መከላከል ክፍል የእሳት ፍተሻ እንዲያደርግላቸው፣ የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ ለዲሲ ግምጃቤት ተከፋይ ከሚሆን የ $150.00 ቼክ ወይንም ጥሬ ገንዘብ ጋር ወደ የእሳት መከላከል ክፍል የእሳት መከላከል ክፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
ይህ መረጃ 1100 4th Street SW 2nd Floor, Washington DC 20024 ላይ ወደሚገኘው የፈቃዶች እና ክፍያዎች ማእከላችን (የመስኮት ቁጥሮች 30 እና 31) መላክ ይኖርበታል።
የፍተሻ ይደረግልኝ ጥያቄዎ በኦንላይን ማስረከብ ከፈለጉ፣ እባክዎ የፈቃዶች እና ፍተሻዎች መተግበሪያን ይጎብኙ። የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ ቪዛ፣ ማስተርካርድ እና ዲስካቨርን እንቀበላለን)።
ፈቃድ በሚታደስበት ጊዜ የእሳት ፍተሻ ማድረግ የሚጠበቅባቸው የንግድ ድርጅቶች ምሳሌዎች:
- የችርቻሮ/ ሸቀጣሸቀጥ ሱቆች
- መጠጥ ቤቶች
- ምግብ-ቤቶች
- የምሽት ክለቦች
- የቀን እንክብካቤ ማእከላት
- የእንግዶች ማቆያ/ ማደሪያ ክፍሎች
- ለብዙ ሰዎች በአንድ ላይ አገልግሎት የሚሰጡ የመኖሪያ ቤት ተቋማት
- የአገልግሎት ጣቢያዎች
- የተሸከርካሪዎች ጥገና ማእከል
- ማንኛውም ሌላ በፈቃድ ሰጪ የከተማው ተቋም የተለየ የንግስ ስራ ድርጅት
የሰራ ፈቃዶች
የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ክፍል የእሳት መከላከል ክፍል ጉዳት ሊያስከትሉ በሚችሉ እና የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ማህበረሰብ፣ ለደንበኞች እና ጎብኚዎች ደህንነት አስጊ በሆኑ የንግድ ስራዎች ላይ የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች፣ ኩባንያዎች እና የንግድ ድርጅቶች ስራዎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እያካሄዱ መሆናቸውን የመቆጣጠር ሀላፊነት አለበት።
ይህንን እውን ለማድረግ፣ የእሳት ደንብ በሚገባ መከበሩን ለማረጋገጥ ግምገማ ሊደረግባቸው የሚገቡ እና ተገቢ ማጣራት ከተደረገ በኋላ ከእሳት ሀላፊው የስራ ፈቃድ ሊሰጣቸው የሚገባ የተለዩ የስራ ክንዋኔ እና አሰራሮች አሉ።
Operational permits are required as specified in the IFC 2012 Edition and the Title 12 DCMR 12H Fire Code Supplement (2013). የስራ ፈቃዶች በእሳት ደንብ ማጠናከሪያ (2013) የ IFC 2012 እትም እና 12 DCMR 12H በሚለው አርእስት ላይ በግልጽ በተቀመጠው ሕግ መሰረት ሊሰጡ ይገባል።
የስራ ፈቃዱ የእሳት መከላከል ክፍሉን የአደገኛ አጠቃቀም ወይንም ማከማቻ የመፈተሽ ዕድል በመስጠት፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ እና ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ስጋቶችን ለይቶ በማወቅ፣ ሁሉም በስራ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ የእሳት እና የህይወት ደህንነት ችግሮች መፍትሄ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል።
ብናኝ የሚፈጥሩ ምርቶች፣ ካርኒቫሎች እና ትርኢቶች፣ አውደርእዮች እና የንግድ ትርኢቶች፣ ኢንዳስትሪያላዊ ምድጃዎች እና የተረፈ ምርት አያያዞችን ጨምሮ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ብዙ ሁኔታዎች የስራ ፈቃድ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የተሟላውን ዝርዝር ለማየት እባክዎ እዚህ ይምረጡ።
የስራ ፈቃዶች የሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ከዲሲ የእሳት እና የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት የእሳት መከላከል ክፍል ማግኘት ይችላሉ፤ አድራሻ 1100 4th Street SW Suite E700, Washington, DC 20024 ስልክ (202) 727-1614።
የ FPD ክፍል የስራ ሰአታት ከ 8:15 AM እስከ 16:45 PM፣ ከሰኞ እስከ አርብ።
የዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ. እባክዎ የፈቃዶች እና ፍተሻዎች ማመልከቻ ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ።
ቪዛ፣ ማስተርካርድ እና ዲስካቨር እንቀበላለን)። እባክዎ ልብ ይበሉ: ማጠናከሪያ ሰነዶች የግድ መጫን አለባቸው።
እባክዎትን ማንኛውንም ተጨማሪ የሰነድ ጥያቄ ወደ [email protected] ይላኩ