Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Cadet Program - Amharic

የእሳት ካዴት ፕሮግራም

የካዴት ፕሮግራም እድሜያቸው ከ 18 እስከ 21 ለሆኑ የዲስትሪክት ኮሎምቢያ ነዋሪዎች  የኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት (DCFEMS) አባላት የመሆን እድል የሚያገኙበት የአንድ አመት ፕሮግራም ነው።  በፕሮግራሙ የጊዜ ቆይታ፣ ካዴቶች የብሄራዊ ረጂስትሪ፣ የእሳት አደጋ ሰራተኛ I ከምኡድማ II፣ እና የአደገኛ ማቴርያሎች ግንዛቤ እና ማሰራት ወረቀት ምስክር ያገኛሉ። ካዴቱ ሁሉንም የኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት ገጽታዎች የሚያይበት እና የሚለምድበት የዲፓርትመንት እሽክርክሪታዊ እንቅስቃሴ ላይ ይሳተፋል።

ብቁነት 

የእሳት ካዴት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ሰዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል:

  • የዲሲ ነዋሪ መሆን አለብዎ
  • ከዲሲ የመንግስት፣ የመንግስት ቻርተር ወይንም የቤተ-ክርስትያን ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት-ቤት በዲፕሎማ ወይንም በ GED የተመረቀ መሆን አለብዎ
  •  እድሜዎ በ 18 - 21 አመት መካከል መሆን አለበት
  • አጠቃላይ ማእከላይ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት-ቤት ውጤትዎ GPA 2.5 መሆን አለበት
  • ቢያንስ ተቀባይነት ያለው- የአሽከርካሪ ተማሪ ፈቃድ ሊኖርዎ ይገባል

ደሞዝ/ጥቅማጥቅሞች

ካዴቶች ፈተናው ካለፉ እና ከተመረጡ በኋላ በአመት $22,526 ደሞዝ ያገኛሉ፣ የ 4 ሰአት ተጨማሪ አመታዊ ክፍያ እና በየሁለት ሳምንቱ የህመም እረፍት ያገኛሉ።
 
ፕሮግራሙ በስኬት ያጠናቀቁ አዳዲስ የእሳት አደጋ ሰራተኛ EMT ምልምሎች አመታዊ የመሻ ደሞዛቸው $48,881 ይሆናል፣ እንዲሁም የ 4.5 ሰአት ተጨማሪ አመታዊ ክፍያ እና በየሁለት ሳምንቱ የህመም እረፍት ያገኛሉ፣ እንዲሁም የጤና እና የህይወት መድህን እና የማህበር ተወካይነት የማግኘት እድል ያገኛሉ።
 

የምልመላ ሂደት

የተመረጡ እጩዎች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል:
  •  የግል ታሪክዎ ማመልከቻ ይሙሉ;
  • ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት፣ FBI, እና ከዩኤስ ፓርክ ፖሊስ ከወንጀል ነጻ መሆንዎ የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ;
  • ከሞተር ተሸከርካሪዎች ዲፓርትመንት የመንዳት መዝገብ ማቅረብ;
  • በፖሊስ እና በእሳት አደጋ ክሊኒክ የአካል ምርመራ እና ስነልቦና ማርመራ ማድረግ;
  • የማጣቀሻ ቼኮችን ማቅረብ;
  • የዩኤስ ዜግነት ማቅረብ; እና
  • የተመረጠ የአገልግሎት ረጂስትሪ ማረጋገጥ (ለወንዶች ብቻ)።

ለእሳት ካዴት ፕሮግራም ማመልከቻ ለማስገባት የሚከተሉት ሰነዶች ማቅረብ ይኖርብዎታል:

  1.     መንጂያ- ፈቃድ ወይንም የመንጂያ- ፈቃድድ ተማሪ ፈቃድ;
  2.     የከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ዲፕሎማ / GED ወረቀት ምስክር; እንዲሁም
  3.     የመጨረሻ የከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ትራንስክሪፕት / GED ትራንስክሪፕት።
ማልከቻዎች ማስገባት የሚቻልበት ጊዜ ሰኔ 01, 2017 እና መስከረም 01, 2017።
 

 

የምልመላ ሀላፊዎች:
 
2000 14th Street NW
Washington, DC 20009
ዋና: 202-673-3330
ቀጥታ: 202-673-3726 ወይንም 202-397-3966