Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Project Safe Place - Amharic

ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ፕሮጀክት

ሁሉም 33 የበኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት የእሳት አደጋ ጣቢያዎች እና የእሳት አደጋ ጃልባዎች  ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ፕሮጀክት አማካኝነት "ደህንነት ቦታ" ቀውስ ውስጥ ለሚገኙ ወጣቶች ለ 24 ሰአታት ያዘጋጃል።

ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ፕሮጀክት ከቀውስ ጋር የተያያዘ እገዛ ለሚፈልጉ ወጣቶች ደህንነት ቦታ የሚያቀርብ ብሄራዊ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ በ ሳሻ ብሩስ የወጣቶች ስራ ይተዳደራል። የበኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት ከ 1992 ጀምሮ በአጋርነት ቆይተዋል።

ሁሉም የበኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች የእሳት አደጋ ጣቢያዎች ልዩ የደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ አርማ ያሳያል። አርማው በእሳት አደጋ ጣቢያው ውጫዊ ገጽታ ላይ ከጎዳናው በግልጽ ሊታይ በሚችል ሁኔታ ተለጥፏል። ማንኛውም ቀውስ ውስጥ የተዘፈቀ ወጣት በ 24 ሰአታት ውስጥ በማንኛውም ሰአት ወደ እሳት አደጋ ጣቢያው በመምጣት ጊዜያዊ መጠለያ እና እርዳታ ማግኘት ይችላል። በእሳት አደጋ ጣቢያው የሚገኙ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ወይንም EMS አቅራቢዎች የወጣቶች መጠለያ እና የደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ቀጥታ መስመር አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል። የሳሻ ብሩስ የወጣቶች ስራ የምክር አገልግሎት ሰጪዎች ወደ የእሳት አደጋ ጣቢያው በመምጣት ለሳሻ ብሩስ መጠለያ እገዛ እና መጓጓዣ ይሰጣል።

የደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ቀጥታ መስመር: (202) 547-7777

ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ የበኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ደንበኛ አገልግሎት ጽሕፈት-ቤት በ (202) 673-3677 ወይንም (202) 673-3678 ይደውሉ; ወይንም ወደ ሳሻ ብሩስ የወጣቶች ስራ ጋር በ (202) 675-9370 ይደውሉ።
ከ TTY ጋር ይገናኙ: 
711