Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Frequently Asked Questions About Fireworks - Amharic

በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ሕጋዊነት ያላቸው ርችቶች የትኞቹ ናቸው?

ከ 20 ኢንች ያነሱ አብለጭላጮች፣ ችቦዎች፣ የሳጥን እሳት፣ ፋውንተይን፣ ኮንስ፣ ዘንግ፣ መርዛማ ያልሆኑ እባቦች፣ በወረቀት የተሰሩ አሻንጉሊቶች፣ ህብር ያላቸው መብራቶች፣ እና የወረቀት ኮፍያዎች።

ዲሲ ላይ ሕጋዊነት የሌላቸው ርችቶች የትኞቹ ናቸው?

እንደ ቼሪ ቦምቦች፣ የክብር ተኩሶች፣ የሮማውያን ሻማዎች፣ የአበቦች ተኩስ፣ እና የከባድ መሳሪያ ተኩስ የመሳሰሉ ፈንጂ እሳቶች ወይንም ርችቶች።

የሆነ ሰው ሕገወጥ ርችቶችን ሲጠቀም ወይንም ሲሸጥ ካየሁ ምን ማድረግ አለብኝ?

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ዜጋ እንደመሆንዎ መጠን፣ ህገወጥ ርችቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ ወይንም ሲሸጡ ካዩ ለዲሲ የእሳት ማርሻሎች ጽሕፈት-ቤት በ (202) 727-1600 ሪፖርት በማድረግ ወዲያውኑ እርምጃ እንዲወሰድ ማስደረግ ይኖርብዎታል።

የሕገወጥ ርችቶች የመጠቀም ቅጣቶች ምንድ ናቸው?

ማንኛውም በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ህገወጥ ርችቶችን ሲጠቀም ወይንም ይዞ የተገኘ ሰው እስከ $1,000 የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና/ወይንም ተጨማሪ የእስር ቅጣት ይጣልበታል።

ርችቶችን ከማን ነው መግዛት ያለብኝ?

ማንኛውም በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኝ ዜጋ ርችቶችን መግዛት ያለበት ፈቃድ ከተሰጣቸው ነጋዴዎች ነው።

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ርችት የሚቸረችሩ ነጋዴዎች ርችቶቹን ከየት ነው መግዛት ያለባቸው?

ማንኛውም ርችቶችን በኮሎምቢያ ዲስትሪክት መቸርቸር የሚፈልግ ነጋዴ፣ ርችቶቹን መግዛት ያለበት ምርቶቹን በእሳት ማርሻል ጽሕፈት-ቤት ካስመረመረ የተፈቀደለት የጅምላ ነጋዴ ነው።የተፈቀደላቸው የርችቶች እና ጅምላ ነጋዴዎች የሚያሳይ ዝርዝር በየአመቱ ግንቦት 25 ከእሳት ማርሻል ጽሕፈት-ቤት መውሰድ ይቻላል።

ልብ ይበሉ: ሁሉም ሕገወጥ የሆኑ ርችቶች በእሳት ማርሻል ጽሕፈት-ቤት እንዲወረሱ እና እንዲወድሙ ይደረጋል። ያስተውሉ።

ዲሲ ላይ ርችቶችን ለመሸጥ ምን አይነት ፈቃድ ያስፈልገኛል?

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የርችት ችርቻሮ ነጋዴ ለመሆን፣ የንግድ ስራ ፈቃድ ከ DCRA የርችቶች ፍተሻ እና ማከማቸት ፈቃድ ደግሞ ከዲሲ እሳት ማርሻል ጽሕፈት-ቤት መውሰድ ይኖርብዎታል።.አንድ ቸርቻሪ እነዚህን ሁለት ፈቃዶች በተጠየቀ ጊዜ ማሳየት ካልቻለ፣ የርችት ምርቶቹ ይወረሳሉ ንግድ ቤቱም ይዘጋል።ሁልጊዜ ሁሉንም ፈቃዶች እና የንግድ ስራ ፈቃዶች በቅርብ ያስቀምጡ።

ማንኛውም በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ላይ ርችቶችን መሸጥ የሚፈልግ ሰው ሁለት ፈቃዶች ማውጣት አለበት:

የሻጮች የችርቻሮ ፈቃድ ከደንበኞች እና ቁጥጥር ጉዳዮች መምሪያ።
ከእሳት ማርሻል ጽሕፈት-ቤት በቦታ ፍተሻ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ የርችት ፈቃድ። የፈቃዱ ዋጋ $50 ነው።

ምርቶቼ በእሳት ማርሻል ጽሕፈት-ቤት ከተወረሱብኝ እኔ እንደ ቸርቻሪ ምን መብቶች አሉኝ?

ቸርቻሪዎች ምርቶቻቸው ከተወረሱባቸው ቀን አንስቶ በ 30 ቀናቶች ውስጥ ወደ የእሳት ማርሻል አቤቱታ ማቅረብ አላቸው።

የተወረሱት የርችት ምርቶች ምንድነው የሚደረጉት?

ሕገወጥ ርችቶቹ ከ 30 ቀናቶች በኋላ እንዲወድሙ ይደረጋል።

ከርችቶች ደህንነት ጋር በተያያዘ ማወቅ ያለብኝ የተወሰኑ መረጃዎች ምንድናቸው?

  • ሁልጊዜ የአጠቃቀም መመሪያዎቹን ያንብቡ እና ይከተሉ።
  • ሁልጊዜ አዋቂ ሰው ከቦታው መለየት የለበትም።
  • ርችቶች መለኮስ ያለባቸውከቤት ውጪ ብቻ ነው ።
  • ሁልጊዜም ርችቶቹን ከተጠቀሙ በኋላ የሚያጠፉበት ውሃ እና አሸዋ ከአቅራቢያዎ አይለዩ።
  • በፍጹም ርችቶችን ለመስራት አይሞክሩ።
  • በአንድ ጊዜ አንድ ርችት ብቻ ይለኩሱ።
  • የተበላሹ ርችቶችን በፍጹም ደግመው አይለኩሱ።
  • ርችቶችን ህጻናት ከማይደርሱበት ቦታ ያስቀምጡ።
  • ርችቶችን ቀዝቃዛ እና ደረቅ በሆነ ቦታ ያስቀምጡ።
  • ርችቶችን በፍጹም ወደ ሌላ ሰው አይወርውሩ።
  • ርችቶችን በፍጹም ኪስዎ ውስጥ አያስቀምጡ።
  • ከሚነዱ ኮኖች እና ፋውንቴኖች ቢያንስ 15 ጫማ ይራቁ።
  • ርችቶችን እንደ ነዳጅ፣ ጋዜጣዎች ወዘተ የመሳሰሉ ተቀጣጣይ ነገሮች አጠገብ አይለኩሱ።
  • ረጥበው የደረቁ ርችቶችን አይለኩሱ።
  • ርችቶችን ያለፊዩዝ የትም ቦታ አይለኩሱ።
  • ሕገወጥ ርችቶችን አይጠቀሙ።
  • የአምራቹ ስም፣ አድራሻ፣ እና ማስጠንቀቂያዎች በግልጽ የተጻፉባቸው እቃዎችን ብቻ ይጠቀሙ።