በአካባቢዎ የሚገኝ የእሳት አደጋ ጣቢያ ለመጎብኘት አስቀድመው ጥያቄ ማቅረብ ይኖርብዎታል። ጉብኙቱ ከ 30 እስከ 40 ደቂቃ ገደማ የሚቆይ ሲሆን የሚከተሉትን ያጠቃልላል:
- ከእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ ተባባሪ ሐኪሞች እና የድንገተኛ አደጋ ሕክምና ቴክኒሻኖች (EMTs) ጋር መገናኘት;
- የእሳት ደህንነት ፕረዘንቴሽን;
- የኢንጂን ቤት ጉብኝት;
- መሳሪያዎችን መመልከት;
- የይቁሙ፣ ይጋደሙ፣ ፊትዎ ይሸፍኑ እና ይንከባለሉ መመሪያ በእሳት አደጋ ሰራተኛ ይብራራልዎታል;
- የተሳታፊዎች የጥያቄ እና መልስ ክፍለጊዜ።
የጉብኝት መስፈርት
- ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ 9 ኤኤም እስከ 11ኤኤም እና ከ 1 ፒኤም እስከ 5 ፒኤም ጉብኝት ለማድረግ ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።;
- ከሶስት (3) ስራ ቀናቶች በፊት የጉብኝት ጥያቄዎ ማቅረብ ይኖርብዎታል;
- አንድ የጉብኝት ቡድን 30 ወይንም ከሰላሳ ያነሱ ተሳታፊዎችን (ህጻንትን እና ሸኚዎችን ጨምሮ) ነው መያዝ ያለበት። ለ 8 ህጻናት 1 አዋቂ ሸኚ ነው መኖር ያለበት።
የእሳት አደጋ ጀልባ ጉብኝቶች
እሳት አደጋ ጀልባ ጉብኝት እያንዳንዱን ኬዝ መሰረት በማድረግ ሊሰጥ ይችላል።
በስልክ ቁጥር (202) 673-3331 በመደወል አንዱን ይጠይቁ
ከ TTY ጋር ይገናኙ: 711