Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Free Smoke Alarms - Amharic

Smoke Alarm

የ A- ሲያ ሱቶን የጭስ ማሳወቂያ ደወል የመስጠት እና የመግጠም ፕሮግራም ሁሉም የዲስትሪክት ኮሎምቢያ ቤቶች በሚገባ የሚሰራ የጭስ ማሳወቂያ ደወል እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚሰራ በመላ ዲስትሪክቱ የተዘረጋ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት ኢኒሼቲቭ ነው። በሚገባ የሚሰሩ የጭስ ማሳወቂያ ደወሎች ህይወት በመታግ የተዋጣላቸው እንደመሆናቸው መጠን እቤት ውስጥ ከሚገጠሙት ነገሮች ሁሉ ወሳኝ እቃወች ናቸው ብለን እናምናለን።

መረጃዎች እንደሚያሳዩን አብዛኞቹ በእሳት አደጋ ምክንያት የሚከሰቱ ሞቶች የጭስ ማሳወቂያ ደወል በሌላቸው ወይንም በአግባቡ የማይሰሩ የጭስ ማሳወቂያ ደወሎች ባዋቸው ቤቶች ነው የሚከሰቱት። በ 2009 ብቻ፣ ዲስትሪክቱ እቤት ውስጥ በተከሰቱ የእሳት አደጋዎች ምክንያት 19 ነዋሪዎችን በሞት ተነጥቋል። ቤት ውስጥ የተገጠሙ በአግባቡ የሚሰሩ የጭስ ማሳወቂያ ደወሎች በሞነሪያ ስፍራዎች የሚከሰት የእሳት አደጋ ሞትን በእጅጉ ይቀንሳል።

የጭስ ማሳወቂያ ደወል ለመቀበል መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:

  • የዲስትሪክት ኮሎምቢያ ነዋሪ መሆንዎ የሚያሳይ ማረጋገጫ ማሳየት አለብዎ።
  • የሚኖሩበት ቤት ባለንብረት መሆን (ተከራይ መሆን የለብዎትም) አለብዎ።
  •  ዲፓርትመንቱ የጭስ ማሳወቂያ ደወል ይገጥማል።

የጭስ ማሳወቂያ ደወሎች የአገልግሎት ጥያቄ ኦንላይን ላይ በማስገባት መጠየቅ ይችላሉ። የጭስ ማሳወቂያ ደወል ቅጽ ለመፈለግ እና ለመሙላት ወይንም ማናቸውም ሌላ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች አገልግሎት ለመጠየቅ የሲደመር ምልክቱን ይጠቀሙ። እባክዎ ለጥያቄዎ ምላሽ ለማግኘት ቢያንስ 24 ሰአታት መጠበቅ እንዳብዎ አይዘንጉ። ለጥያቄዎች እና አስተያየቶች በ (202) 727-1614 ወይንም በ (202) 673-3331 ይደውሉ።

ማስታወሻ: የኮሎምቢያ ዲስትሪክት እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት በተጠየቀው ቀን እና ሰአት ምላሽ ለመስጠት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል። የእርስዎን የጭስ ማሳወቂያ ደወል ለመግጠም የተመደቡት ክፍሎች መኖሪያው ቤት መሆኑን ለማረጋገጥ ከእርስዎ ጥያቄ ጊዜ በፊት ከ 30 እስከ አንድ ሰአት አስቀድመው ይደውላሉ። ይሁን እንጂ፣ የጭስ ማሳወቂያ ደወሉን ለመግጠም የተመደበው ክፍል የድንገተኛ አደጋ ጥሪ ከደረሰው፣ መጀመሪያ ምላሽ መስጠት ያለበት ለድንገተኛ አደጋው ነው። ይህ ማለት ዘግይተው ሊመጡ ወይንም ቀጠሮውን ሊሰርዙት ይችላሉ ማለት ነው። ድንገተኛ አደጋው ካበቃ በኋላ እንደገና ቀጠሮ ለማስያዝ ይደውላሉ።
ከ TTY ጋር ይገናኙ: 
711