Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

fems

Fire and EMS Department
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Tour Your Local Fire Station! - Amharic

firefighters and emergency medical professionals speaking to kids at a firestation

በአካባቢዎ የሚገኝ የእሳት አደጋ ጣቢያ ለመጎብኘት አስቀድመው ጥያቄ ማቅረብ ይኖርብዎታል።  ጉብኙቱ ከ 30 እስከ 40 ደቂቃ ገደማ የሚቆይ ሲሆን የሚከተሉትን ያጠቃልላል:

  • ከእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ ተባባሪ ሐኪሞች እና የድንገተኛ አደጋ ሕክምና ቴክኒሻኖች (EMTs) ጋር መገናኘት;
  • የእሳት ደህንነት ፕረዘንቴሽን;
  • የኢንጂን ቤት ጉብኝት;
  • መሳሪያዎችን መመልከት;
  •  የይቁሙ፣ ይጋደሙ፣ ፊትዎ ይሸፍኑ እና ይንከባለሉ መመሪያ በእሳት አደጋ ሰራተኛ ይብራራልዎታል;
  • የተሳታፊዎች የጥያቄ እና መልስ ክፍለጊዜ።

የጉብኝት መስፈርት

  • ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 9 ኤኤም እስከ 11ኤኤም እና 1 ፒኤም እስከ 5 ፒኤም ጉብኝት ለማድረግ ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።;
  • ከሶስት (3) ስራ ቀናቶች በፊት የጉብኝት ጥያቄዎ ማቅረብ ይኖርብዎታል;
  • አንድ የጉብኝት ቡድን 30 ወይንም ከሰላሳ ያነሱ ተሳታፊዎችን (ህጻንትን እና ሸኚዎችን ጨምሮ) ነው መያዝ ያለበት። 8 ህጻናት 1 አዋቂ ሸኚ ነው መኖር ያለበት።

የእሳት አደጋ ጣብያዎች ካርታ ይመልከቱ።.

የእሳት አደጋ ጀልባ ጉብኝቶች

እሳት አደጋ ጀልባ ጉብኝት እያንዳንዱን ኬዝ መሰረት በማድረግ ሊሰጥ ይችላል።

በስልክ ቁጥር (202) 673-3331 በመደወል አንዱን ይጠይቁ
 

TTY ጋር ይገናኙ: 711