በዚህ ሰነድ ውስጥ የሚገኘው መረጃ ለሁሉም ከዲሲ እሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች ዲፓርትመንት የእሳት መከላከል ክፍል የፍጆታ ርችቶች ፈቃድ ለማግኘት የሚጠይቁ አመልካቾችን ያገለግላል።
በአንድ በኩል የፍጆታ ርችቶች ማከናወኛ ፈቃዶች ጥያቄዎች ጉዳይ ብቁ እና ስርአት ባለው አካሄድ እንዲሁም ያለምንም መዘግየት ማከናወን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህብረተሰቡን፣ የሻጮችን፣ እና የተቆጣጣሪዎችን ደህንነት ማረጋገጥ እንዲሁም ህጎችን፣ ደንቦችን እና ስነስርአቶችን አክብሮ መስራት የእሳት መከላከል ክፍል ፖሊሲ ነው።
የማመልከቻ ጊዜው ሜይ 22 የሚከፈት ሲሆን የሚያበቃበት ቀን ደግሞ ጁን 22, 2018 ነው።.
ጊዜያዊ እና ቋሚ የርችቶች ፈቃዶች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠይቃሉ:
ከደንበኞች እና የቁጥጥር ጉዳዮች መምሪያ የሚከተሉትን ማግኘት ያስፈልጋል:
- ለጊዚያዊ መሸጫው የህንጻ ፈቃድ
- ጊዜያዊ መብራት እና/ወይንም ጀነሬተር የሚያስፈልግ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፈቃድ።
ከጊዜያዊ መሸጫ ወይንም የንግድ ስራ ቦታ ላይ ርችቶችን ለመቸርቸር የፈቃድ ማመልከቻ በሚያስገቡበት ጊዜ ዋናውን እና ሁለት ቅጂዎች ለዲሲ የእሳት እና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የእሳት መከላከል ክፍል መቅረብ አለባቸው:
- የመንጃ ፈቃድ፣ ኮሎምቢያ ዲስትሪክት፣ የግዛት ፈቃድ ወይንም ይሁኝታ
- ርችቶች ይሸጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ሰራተኞች ዝርዝር (ስሞቻቸው እና እድሜያቸው)
- መሸጫ ቦታው ከመውጪያ በሩ ትይዩ መሆኑ፣ ከህንጻዎች፣ ከጎዳናዎች፣ እና ከሌሎች ግንባታዎች ያለውን ርቀት፣ የሚያሳይ የቦታው ካርታ
- አመልካቹ በህንጻው ርችቶች እንዲሸጥ ፈቃድ ከሰጠው ባለህንጻ ሕጋዊ ማረጋገጫ የተደረገላቸው ሁለት (2) ቅጂዎች
- DCMR 12H F-5609.5.9 2013 ገንዘባዊ ሀላፊነት፣ ርችቶች ለማከማቸት ወይንም ለመቸርቸር ፈቃድ የሚጠይቅ ግለሰብ ወይንም የንግድ ድርጅት ወለድ ሳይጨምር ቢያንስ የ $100,000 መጠን ያለው ኮርፖሬት የመተማመኛ ቦንድ ወይንም ተመሳሳይ መጠን ያለው የህዝብ ካሳ መድህን ፖሊሲ ለእሳት ሀላፊው ወይንም ለተወካዩ ማስገባት ይኖርበታል፤ እነዚህ በፈቃዱ መሰረት በሚከናወኑ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ምክንያት በሰዎች ወይንም በንብረት ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች ካሳ የሚያስከፍል ውሳኔ በፍርድቤት በሚሰጥበት ጊዜ ካሳ ለመክፈል የሚውሉ ናቸው።
- ይህ ክፍል በሁሉም ቋሚ እና ጊዜያዊ የመሸጫ ሱቆች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
- የተሞላው ማመልከቻ ዋናው እና ቅጂው፣ ሁሉም አስፈላጊ አባሪዎች፣ እንዲሁም ለዲሲ ግምጃቤት መከፈል ያለበት $250.00 የፈቃድ ክፍያ በቼክ፣ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በክረዲት ካርድ በያስረከብ የጸደቀውን የርችቶች ዝርዝር ቅጂ ይቀበሉ። (የሁሉም የኦንላይን ማመልከቻዎች ክፍያ መከፈል ያለበት በክረዲት ካርድ ብቻ ነው)
- የፈቃድ ማመልከቻው ትክክል መሆኑ ለማረጋገጥ ግምገማ ይደረግበታል ከዛም ጊዜያዊው የመሸጫ ቦታ ወይንም የንግድ ስራ ስፍራው ፍተሻ ከተደረገበት በኋላ ይጸድቃል።. ሁሉም በ DCRA የተሰጡ ዋና ፈቃዶች፣ የንግድ ስራ ፈቃዶች፣ እና የቦታ ማረጋገጫ በፍተሻው ጊዜ የግድ በቦታው መገኘት አለባቸው። የፍተሻ ቀጠሮ ለማስያዝ እባክዎ በ (202) 727-1614 ይደውሉ።
የርችቶች ፈቃድ አገናኞች 2018
የቋሚ ችርቻሮ ንግድ ስራ ፈቃድ ማመልከቻ - https://dcwebforms.dc.gov/fems/permit1
- የማመልከቻ አይነት:
- የፈቃድ አይነት: የርችቶች ችርቻሮ ቦታ - ቋሚ
የጊዜያዊ መሸጫ ቦታ ፈቃድ ማመልከቻ - https://dcwebforms.dc.gov/fems/permit1
- የማመልከቻ አይነት:
- የፈቃድ አይነት: የርችቶች ችርቻሮ ቦታ - ጊዜያዊ
Contact TTY:
711